by ጭስዬ ( 112 ) 4 years ago

ዋሻ ሙድ

ትዕቢት ትዕቢት ብሎክ፣ ውጣና ይዋጣልን ሲሉክ እምቢየው ማለት።

ፊሪኩ እየጠጣን እያለ ሙዳችንን አበላሽቶ ላስቀይመው ስል ዋሻ ሙድ አልሆነም?

by Lexa ( 80 ) 4 years ago

መሶቦ

ሚዛን ላይ ሲወጣ እንደ ሲሚንቶ ከረጢት ከ50 ኪሎ በልጦ የማይውቅ ሰው።

ለምን ትለካለህ መሶቦነትህን እያወከው!

by Markos ( 341 ) 4 years ago

ጀለሶችና ጀለሳት

Ladies and gentleman

ጀለሶችና ጀለሳት, እንኳን በሰላም ወደ አመታዊ የከፍታ ጉባኤ መጣችሁ::

by Orion ( 120 ) 3 years ago

ሩፍቶፕ / Rooftop

አፍ

Period ላይ ነኝ ብላ ሩፍቶፕ ፈቀደችልኝ::

by Tupilicios ( 140 ) 3 years ago

የመጠነ ቁስ ተመራማሪ

ባላየ ባልሰማ የማያውቀው ርዕስ ላይ የሚዘባርቅ ሰው

ግርማ ከዱባይ ሲመለስ የመጠነ ቁስ ተመራማሪ ሆኖ አላስወራ አለን።

by scaravance ( 1524 ) 3 years ago

ጥሬአርጉትሊ

Relatively በአማርኛ / የአብስሉትሊ(Absolutely) ተቃራኒ

ማሽላ ተወደደ እንጂ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከ 1950ዎቹ ጥሬአርጉትሊ ተሻሽሏል::

by scaravance ( 1524 ) 3 years ago

በላይነሽ አመዴ

ድሮን/Drone በአማርኛ

ልመጣ ብል ሸገር በመላ በዘዴ - ባይን ፍቅር ጣለችኝ በላይነሽ አመዴ

by abush ( 318 ) 2 years ago

ቦሌ ስጋ ቤት Index

አብይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምን ያህል እንዳደገ የሚለካበት መሳርያ::

ቦሌ ያሉ ስጋ ቤቶች ተጨናንቀዋልና: ይህ የሚያሳየን 110ሚልዮኑ ህዝብ ጥሩ አቋም ላይ እንዳለ ነው::

by danny ( 119 ) 4 years ago

ላሽ

ማምለጥ: አለመሄድ

ዛፓው ከች ሳይል ላሽ እንዲሉ ነገራቸው:

by barud ( 13 ) 4 years ago

ተነፋነፍ

ተነፋ..በረጅሙ

ተነፋ..ነፍ ሱሪ ቢገዛ እንደምያምርበት ነግሬው ላሽ አልኩኝ: እናቱን::