by abush on 2 years ago

ቦሌ ስጋ ቤት Index

አብይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምን ያህል እንዳደገ የሚለካበት መሳርያ::

ቦሌ ያሉ ስጋ ቤቶች ተጨናንቀዋልና: ይህ የሚያሳየን 110ሚልዮኑ ህዝብ ጥሩ አቋም ላይ እንዳለ ነው::

by abush on 3 years ago

ማር ጨረቃ

በCOVID ወቅት ያገቡ ሰዎች የሚያደርጉት በበጀት የተመጠነ ጫጉላ or honeymoon

ማርቲ እና ሃብትሽ እኮ ለማር ጨረቃቸው ወደ ወለጋ ሄዱ::

by abush on 4 years ago

ኳስ

ድፍረት / Balls

ኳሱን ቤት ጥሎ መጥቶ ክራሹን ሳያዋራት ተመለሰ::

by abush on 4 years ago

phack

ሃሰተኛ ነቢይ የተባረከ ሲያስመስል

phack ኢችአዘርቱጌዜር

by abush on 4 years ago

ሁለተኛ እንዳትደውይልኝ

ገደል ግቢ

እሷ: የእርሶ ምክር በጣም ረድቶናል: አመሰግናለው:: በመጨረሻ ሊሉት የሚፈልጉት ነገር ካለ... እሳቸው: ሁለተኛ እንዳትደውይልኝ

by abush on 4 years ago

ፈርቅ

በስውር ዋጋ ላይ ሚጨመር ትርፍ ክፍያ : additional hidden payment

ባለፈው ሲሚንቶ ግዛልኝ ብዬው ከባለሱቁ ተስማምቶ ከባድ ፈርቅ ይዞብኝ አገኘሁት

by abush on 4 years ago

ሽመለስ

ሆደ ሰፊ : ቻይ

እሱ ሽመለስ ነገር ነው: እንዲህ ስትጫወትበት ለምን እንደማይፈታት እንጃ::

by abush on 4 years ago

ቅል

ለወደዳት ቺክ ከሚገባ በላይ የሚያደርግ ልጅ: simp

ሰሌ : ባለፈው ሳምንት መኪና ገዛውላት: ለ እናቷ ደሞ አሪፍ ሽቶ : ግን እያካበደች ነው እስካሁን እምቢ ትላለች: ዳኒ: አባቴ! አንደኛ ቅል ነሽ እኮ አንቺ::

by abush on 4 years ago

በዩ

በየአይነት - ምግብ (veggie combo)

አንድ በዩ ና አንድ ሸክላ ጥብስ አርግልን::

by abush on 4 years ago

አንጃይተር

የአንጀት ሞተር ብልሽት : also A fancy way of saying anxiety.

ዛሬ አይጃይተሬ ፈልቶብኝ ከቤት ሳልወጣ ዋልኩ::