by dibe ( 449 ) 4 years ago

ማሳመር : ማማር : ማስዋብ

አርብ ማታ ፏ ብላ እንድትጠብቀኝ ነገርኳት

by abush ( 318 ) 4 years ago

ይብራብኝ

ይለፈኝ : not interested,

አሪፍ ጊዜ እንደምታሳልፉ አቃለው ግን ዛሬ ይብራብኝ::

by abush ( 318 ) 4 years ago

ኢትዮ ጣልያን

ፓስታ በእንጀራ

ምሳ አሪፍ ኢትዮጣልያን ከበላህ ስለ እራት ማሰብ የለብህም::

by scaravance ( 1524 ) 4 years ago

ሚሊሽያ

ጎመን በአይብ

አልማዝ እስኪ አንድ ሚሊሽያ ከች አድርጊ

by Ye bele ( 13 ) 4 years ago

ልጅቷን አርፋታለሁ ፎንቃዬ ነበረች ላበስላት ትምሮ ቤቷ መረሽኩ እሷ ግን ገጀለች

ልጅቷን አውቃታለሁ የማፈቅራት ልጅ ናት ላሳምናት ትመህርት ቤቷ ሄጄ ነበር እሷ ግን እምቢ አለች

by AmanJK7 ( 13 ) 4 years ago

ፍሙ

ሲጋራ

ፍሙ ጠብሰን እንምጣ እስኪ

by Dagi Teferi ( 308 ) 4 years ago

ፈዋ ልወፈስ

ምግብ ልብላ

by kibrom ( 78 ) 4 years ago

አስጌ

በቆሎ ፍሬ ሚያክል አሪፍ ጥርስ ያለው/ያላት

አሊ እኮ ያን ወላቃ ጥርሱን አስጌ አስደረገ::

by kibrom ( 78 ) 4 years ago

ማፊ

እንግሊዝኛን አስገድደው የሚደፍሩ ሰዎች

እኛ ሰፈር ማፊ የተባሉ ወንድና ሴት አሉ ሁለቱም 3 ፍሬ እንግሊዝኛ ቃላት ነው የሚያውቁት ግን በየሰከንዱ ካልጠሯቸው ማውራት ስለማይችሉ: በነሱ ስም ስየምነው::

by abush ( 318 ) 4 years ago

በዩ

በየአይነት - ምግብ (veggie combo)

አንድ በዩ ና አንድ ሸክላ ጥብስ አርግልን::