by
abush ( 318 )
4 years ago
አይነፋም
ደባሪ: አሪፍ ያልሆነ: so so
ምግቡ እንዳስተዋወቁት አይደለም: አይነፋም: 50 ብር ማውጣቴ ጸጸተኝ::
by
dibe ( 449 )
4 years ago
መቀመጥ
ጫት ለመቃም መሄድ
አብዲ ከ7ሰአት እስከ 9:30 ስለሚቀመጥ 10 አካባቢ ነው መድረስ ያለብን::
ሰገጤ
አሪፍ የከተማ ምግባር ማይገባው: የገጠር ልጅ
እረ እሱ ሰገጤ ነው: ከአስተናጋጆች ጋር ሁሌ እንደተከራከረ ነው::
ዝገቴ ቡርቃ
ሰው ማዛግ ማይደክመው/ማት
ኧረ ቶሎ ተፋታው/ታት። ጀለስ እኮ ዝገቴ ቡርቃ ነው/ናት
ብስቋጥ
Basketball
Elias ና ግቢ ሄደን ብስቋጥ እንጫወት
አራገፍክ/ሺ
አቅራራ
መኪና ይዣለው ብለህ በጣም አራገፍክ ታውቆሀል ግን ?