by XghostX ( 42 ) 4 years ago

ሸከቴ

ረጂም የእግር መንገድ የሚያበዛ ሰው

ስማ ሰይፈ እኮ ትላንትናም ሲሸክት ዋለ።

by ጣጱጠስ ( 178 ) 4 years ago

ሰሎሎሚሊሊ

Short for - ስድስት ኪሎ ሚኒሊክ

የፒያሳ ታክሲ ስትጠብቅ አንዱ ረዳት ፊትህ ቆሞ : ሰሎሎሚሊሊ

by ጭስዬ ( 112 ) 4 years ago

ኬሪያ

መስጠት ሙዷ የሆነች ቸከስ( እንኩ በሞቴ ሚሏት አይነት)

ኧረ ቺኳ ኬሪያ ነገር ናት ትቅርብክ ለሚስትነት አትሆንም።

by mikihaile ( 257 ) 3 years ago

ወፍትነት

Latest version of "ወፍ"[ምንም የለም]

ጨላ ወፍትነት ነው ዛሬ

by scaravance ( 1524 ) 2 years ago

ፈቃዱ አንጥረኛው

Will Smith

ጋሽ ፍቄ ክሪስ ሮክን ሲመታው ነው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተናጋው፡፡

by danny ( 119 ) 4 years ago

ስከሳ

አንድን ሰው ለማሳመን የሚደረግ የተጋነነ ወሬ

ዳኒ ካፌ ቀጥሮኝ ስለ ነፋት ቺክ ንብረት ሲሰክሰኝ ዋለ::

by Markos ( 341 ) 4 years ago

መኮመት

Comment መስጠት

አረ ወዮ youtube ላይ ልኮምት ስንቀዥቀዥ ተደፍቼ ነበር::

by mister ( 36 ) 4 years ago

ሾዳ

ጫማ

ድሮ 1 ሾዳ አመት ይቆይ ነበር አሁን ወርም አይበረክትም::

by abush ( 318 ) 4 years ago

አዛ

ማስደበር : ስራ ማስፈታት : ጊዜ ማስባከን

ሃብትሽ ለቁም ነገር እንደሚፈልገኝ ቀጥሮኝ አዛ አርጎኝ ለቀቀኝ::

by abush ( 318 ) 4 years ago

ሳተኝ

እድሉ ይለፈኝ: ይብራብኝ .. miss me

አባቴ! የሷ ዳቦማ ይሳተኝ::