by Markos ( 341 ) 4 years ago
የቤቱ አየር
ደንበኛ መስለው: ጠረጴዛ ይዘው አገልግሎት የሚጠቀሙ ግን በባለቤቱ የተተከሉ
በራሴ ችሎታ ያገነዋት መስሎኝ ቤት አንሂድ ስላት አሁን አልወጣም አለችኝ: ለካ የቤቱ አየር ናት
by mister ( 36 ) 4 years ago
አስጨራሽ
መኪና ካቆምክበት አውጥተህ ልትሄድ ስትል.. የሞተሩን ድምጽ ሰምቶ: "ጎማውን ጨርስ.. ጨርስ" እያለ ከተደበቀበት: መኪናህን ሳይጠብቅ 5ብር ሊቀበልህ የሚመጣ: የመንደር ህገወጥ "ፓርኪንግ" አገልጋይ::
ለአስጨራሾች ብዬ 5ብር መሰብሰብ ጀምሬአለው
by danny ( 119 ) 4 years ago
አዲባስ - adibas
Adidas ለኢትዮጵያውያን አርቲስቶችና official_ች የፈጠረው brand line.
ሳንቾ ሰሞኑን አርጋ ምትዞረው አዲባስ ቱታ አንደኛ ናት::